top of page

Belachew Yimer

Client:

painter

Year:

ተወለዱ በ18 62 ዓ.ም በ19 60 ዓ.ም አርፈዋል

ሠዓሊ በላቸው ይመር በ 18 62 ዓ.ም ተወለዱ በ19ኛ ምዕት ዓመት መገባደጃ ከተነሱት ግንባር ቀደም ሠዓልያን ዝነኛ የነበሩ በላቸው ይመር ፣ ትውልዳቸው የሚነሳው ከጎጃም ጠቅላይ ግዛት ብቸና አውራጃ ፣ የጠም አቦ አጥቢያ ነው ።
ሠዓሊው በላቸው ይመር ሙያቸውን ያዳበሩት በዘልማድ ሲሆን የፈጠራ ችሎታቸውን የሚያንፀባርቁ በርከት ያሉ የሥዕል ሥራዎች ትተዋል ።
በኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ታሪክ በተለይ የሚወሱበት የንግሥት ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ያደረጋቸው ጉዞና ቀዳማዊ ምኒልክን ስለመውለዷ የሚያሳየው ሥዕላዊ ተረካቸው ነው ።
ሌላው ከዓድዋ ጦርነትና ከንግሥተ ሳባ ጉዞ በተጨማሪ ፣የአውሬ ማኀበር ፣ የአይጥና ድመት ጋብቻ ፣ የጌዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፣ የሐረር ቅድስት ሥላሴ ፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ፣ የመተማ ጦርነት ይገኙበታል ።
ሌላው በላቸው ይመር ጎሹ በንግሥት ነገስታት ዘውዲቱ ጊዜ ሥዕል እየሳሉ በመሸጥ መኖር እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳዪ የጥበብ ሰው ናቸው ።
በላቸው ይመር ሌላው የሚጠቀሱት በወራሪዎች ጣሊያውያን ላይ በዓድዋ ጦርነት የተገኘውን ድል በሚያሳዩበት ሥዕሎቻችው ነው ።
በሥዕሉ ጐልተው ከሚታዩት ከጠቅላይ አዝማቹ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በተጨማሪ አዝማቾች ፣ መካከል ፈታውራሪ ገበየሁ ፣ ራስ መንገሻ ፣ ራስ አሉላ፣ ራስ አባተ፣ ደጃዝማች ባልቻ ይጠቀሳሉ ። ከአዝማሪዎች መካከልም አዝማሪ ፃዲቄ እየሸለለችና እየፎከረች ሰታዋጋ የሚያሳይ ሥዕልም የዘመኑ ትሩፋት ነው።
አዝማሪዎች ለኢትዮጵያ ሠራዊት ይሰጡት የነበረው ወኔ ቀስቃሽ አዝመራ ጉልህ ነበር ።
ስለነዚህያ አዝማሪዎች ቤርክሌይ ከጉዞው ጋር አያይዞ የጻፈው የሚጠቀስ ነው።
<<........በሠራዊቱ መሀል አዝማሪዎች አብረው ይዘምታሉ ። በዚያ ሁሉ ሁካታ አዝማሪዎች ዘማቹን እያጫወቱ ይሄዳሉ ።
አብሮአቸው የሚጓዘው ሠራዊትም ለአዝማሪዎቹ ግጥም ይነገርላቸዋል ።
አዝማሪዎቹ የደከመውን በግጥም እያበረታቱ ይጓዛሉ ።>> በዚያን ጊዜ ነው አዝማሪ ፃዲቄ ፦
<< ወንድሜ ራበህ ወይ ? ወንድሜ ጠማህ
ወይ አዎን የናቴ ልጅ እርቦህ ጠምቶሃል
ታዲያ የናቴ ልጅ አዳኝ ወፍ አይደለህም ወይ ?
ግፋ ብረር ወደፊትህ ሂደህ ጠላትህን አትበላም ወይ ?
ግፍ ወደፊት ከበዓሉ ቦታ ፈጥነህ ድረስ የምታደርገውን ሥጋ የማቆራርጥልህ እኔ ነኝ
ግፋ የናቴ ልጅ ወሃ ጠምቶሃል ጠጅ ብታጣ ደሜን እንድትጠጣ እሰጥሃለሁ >> እያለች እየሸለለችና እየፎከረች ያዋጋችው ፤
በላቸው ይመር ጎሹም በሥዕሉ ገበታ ያኖረው ።
ሌላው በላቸው ይመር ጎሹ በንግሥት ነገስታት ዘውዲቱ ጊዜ ሥዕል እየሳሉ በመሸጥ መኖር እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳዪ የጥበብ ሰው ናቸው ። በላቸው በጊዜው በባዶ እግራቸው የሚሔዱ ቢሆንም ስራዎቻቸው በአሁኑ ጊዜ ኦስትሪያ ቬና ፡ ጀርመን ፡ጣሊያን በሚገኙ ሙዜየሞች ይገኛሉ ።
በ19 33 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ልዩና ታሪካዊ ዓመት ነው።
ወራሪው የፋሺስት ጣሊያንን ሠራዊት ከአምስት ዓመታት ተጋድሎ በኋላ የተወገደበት ፣የሚያዝያ 27 ቀን የድል ብሥራት የታወጀበት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ።
የአድዋውን ድል በጥበባቸው የዘከሩት ሠዓሊው በላቸው ይመር ፣ ለሁለተኛው የጣሊያን ጦርነት በድል መጠናቀቅም የሚያሳይ ሥዕልም ነው ።
19 40 ዎቹ አጋማሽ በላቸው ይመር በከፈቱት የራሳቸው ስቱዲዮ ሥራቸውን ሲያከናውኑ በእንጦጦ በሚገኘው አብያተ ክርስቲያንናትም በሥዕሎች በማስዋብ በኩል ከሌሎች ሠዓሊያን ጋር ተሳትፈዋል ።
ሌላው ልጆቻቸው ብቻ ሳይሆኑ የልጅ ልጆቻቸው ሁሉ ሠዕሊያን ናቸው ።
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በስማቸው ቴምብር አሳትሞላቸዋል።
ሠዓሊ በላቸው ይመር ጉሽ በተወለዱ በ18 62
ዓ.ም በ19 60 ዓ.ም አርፈዋል ።
<< አንድንድ የታወቁ የኢትዮጵያ ሠዓሊዎች አጭር የሕይወት ታሪከ 18 62 -19 50 ዓ.ም Short Biographics of Some well -Know Ethiopian Artists 18 69 -19 57 >> በሚል ርዕስ ቦታዬ ታደሰ በተዘጋጀው መደበል ላይ በቀዳሚነት የተጠቀሱት በላቸው ይመር ናቸው ። 18 62 ዓ.ም ሠዓሊ በላቸው የተወለዱበት ዓመት በመሆኑ ከ19ኛው ምዕት ዓመት አጋማሽ ወዲህ ላለው የኢትዮጵያ የሥዕል ታሪክ መነሻም ሆነዋል ።

bottom of page